የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ ስምምነት ተፈራረሙ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ ስምምነት ተፈራረሙ።
አርቲስት እፀህይወት አበበ የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆነች።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና አኮያ ፕሮፐርቲስ የደንበኞቻቸውን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።
ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት፣ የአየር መንገዱን የሽልማት መርሃ-ግብር (ShebaMiles) ከሪል እስቴት ግብይት ጋር የሚያስተሳስር ስምምነት ተደርጓል።
በዚህ ስምምነት መሰረት በአኮያ ፕሮፐርቲስ እየተገነቡ ያሉ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን የሚገዙ ደንበኞች፣ የስታር አሊያንስ (Star Alliance) አባል ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ የጎልድ አባልነት ሽልማት በክብር ያገኛሉ። ይህም ደንበኞች በኢንቨስትመንታቸው ልክ የአየር መንገዱን ጥቅማጥቅሞች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እና የሪል እስቴት ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተመልክቷል።
በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ አኮያ ፕሮፐርቲስ በተለያዩ ፊልሞችና የጥበብ ስራዎቿ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈችውን አርቲስት እፀህይወት አበበን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በይፋ አስተዋውቋል። አርቲስቷ የድርጅቱን ገፅታ በመገንባትና የምርት ስሞቹን ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ስራዎችን እንደምትሰራ ተገልጿል።
ከ230 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረው አኮያ ግሩፕ፣ በውስጡ የተለያዩ ታላላቅ ድርጅቶችን አቅፎ የያዘ ግዙፍ ተቋም ነው። ከእነዚህም መካከል፦
Related Posts
July 20, 2026
ታሪካዊው ምሽት በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ — ስፔን 23ኛውን የዓለም ዋንጫ አነሳች
ብዙ ሳምንታት ጉጉት ፍፃሜውን አግኝቶ ስፔን የዓለምን እግር ኳስ የበላይነት ስትቆጣጠር፣ ይህንን ታሪካዊ የድል ምሽት ኮካ ኮላ…
June 12, 2026
23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ መከፈትን ምክንያት በማድረግ ኮካ ኮላ ልዩ የመክፈቻ ምሽት አዘጋጀ
በዕለቱ የተገኙ የክብር እንግዶች በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል የተደረገውን አጓጊ የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ…
December 26, 2025
የማይረሳ ጉዞ፣ የማይጠገብ ትዝታ! ከፋንታ ጋር የፋንታ ሲኒማ ቱር
ከምስራቅ እስከ ደቡብ፣ በየዩኒቨርሲቲው በፋንታ ጣፋጭ መጠጦች እና ሲኒማ እየተዝናናችሁ አብራችሁን ለተሳተፋችሁ ተማሪዎች…









