23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ ኮካ ኮላ ያዘጋጀው ልዩ የመክፈቻ ፕሮግራም ትላንት ማታ ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ።
በዕለቱ የተገኙ የክብር እንግዶች በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል የተደረገውን አጓጊ የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ በዲኤስቲቪ (DStv) ተባባሪ አዘጋጅነት በትልቅ ስክሪን በአንድነት ተከታትለዋል።
ከዓለም ዋንጫ ጋር የ50 ዓመታት ረጅም የታሪክ አጋርነት ያለው ኮካ ኮላ (Coca-Cola) ያዘጋጀው ይህ ምሽት፣ የስፖርት አፍቃሪያንን እና ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች በታላቅ ስሜት ያገናኘ ነበር።
ከተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ጎን ለጎንም በዕለቱ የተገኙት ታዳሚዎች በተለያዩ አዝናኝ ስፖርታዊ ጨዋታዎች፣ ማራኪ የሙዚቃ ትዕይንቶች እና ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ምሽቱን በደስታ ሲያደምቁት አምሽተዋል።
Related Posts
July 20, 2026
ታሪካዊው ምሽት በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ — ስፔን 23ኛውን የዓለም ዋንጫ አነሳች
ብዙ ሳምንታት ጉጉት ፍፃሜውን አግኝቶ ስፔን የዓለምን እግር ኳስ የበላይነት ስትቆጣጠር፣ ይህንን ታሪካዊ የድል ምሽት ኮካ ኮላ…
December 26, 2025
የማይረሳ ጉዞ፣ የማይጠገብ ትዝታ! ከፋንታ ጋር የፋንታ ሲኒማ ቱር
ከምስራቅ እስከ ደቡብ፣ በየዩኒቨርሲቲው በፋንታ ጣፋጭ መጠጦች እና ሲኒማ እየተዝናናችሁ አብራችሁን ለተሳተፋችሁ ተማሪዎች…
July 28, 2025
“ዓለም ሲኒማ በመገናኛ“ በድምቀት ተመርቆ ተከፈተ፡፡
ለ22 ዓመታት ለሲኒማ ኢንዱስትሪው ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረከተው ዓለም ሲኒማ አሁን ደግሞ ለመገናኛ እና አካባቢው የፊልም…



